Abstract:
የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት የማንበብ ብልሃቶች አጠቃቀም ከማንበብ ተነሳሽነት ጋር ያላቸው
ተዛምዶ፤ ከጾታ አንጻር መፈተሽ ነው፡፡ ጥናቱ ተዛምዷዊ ሲሆን፣ የተካሄደው በማዕከላዊ ጎንደር ዞን
በጎንደር ከተማ ከሚገኙ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ በፋሲደለስ ቁጥር ሁለት አጠቃላይ
ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ ነው፡፡ የምርምር ቦታው በአመቺ የናሙና ስልት የተመረጠ ሲሆን
ተሳታፊዎች እና የክፍል ደረጃው በተራ የእጣ ናሙና ስልት ተመርጠዋል፡፡