mirage

የአስራ አንደኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መምህራን፣ ክሂሎችን አቀናጅቶ የማስተማር አተገባበር ፍተሻ (በነቀምት እና በአንገር ጉትን የመንግስት መሰናዶ ትምህርት ቤት ተተኳሪነት)

DSpace Repository

Show simple item record

dc.contributor.author ደሳለው, ሞገስ
dc.date.accessioned 2023-02-14T08:50:58Z
dc.date.available 2023-02-14T08:50:58Z
dc.date.issued 2012-06-15
dc.identifier.uri http://hdl.handle.net/123456789/5542
dc.description.abstract ይህ ጥናት ገላጭ ስልትን ተከትሎ የተሰራ እና በዓይነቱዓይነታዊ እና መጠናዊ የሆነ ጥናት ነው፡፡የጥናቱ ተሳታፊዎችም ፡- በምስራቅ ወለጋ ዞን ፣ በነቀምት እና በአንገር ጉትን የመንግስት የመሰናዶ ትምህርት ቤት ፣ በ2011 ዓ.ም በአስራ አንደኛ የክፍል ደረጃ አማርኛ ቋንቋን በማስተማር ላይ የሚገኙ በጥቅል የናሙና ዘዴ የተመረጡ 5 መምህራን እንዲሁም በዚሁ የክፍል ደረጃ የሚማሩ ከ519 ተማሪዎች መካከል በቀላል እድል ሰጭ የናሙና ዘዴ የተመረጡ 130 ተማሪዎች ተጠኝዎች ሁነዋል፡፡በመሆኑም በመምህራን የክፍል ውስጥ ምልከታ ፣ በተማሪዎች የጽሁፍመጠየቅእና በሰነድ ፍተሻ(የአስራ አንደኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ የመምህር መምሪያ መጽሀፍ) አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች ተሰብስበዋል፡፡የጥናቱ ዋና ዓላማም ፡- የነቀምት እና የአንገር ጉትን የመንግስት መሰናዶ ትምህርት ቤት፣ የአስራ አንደኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መምህራን፣ክሂሎችን አቀናጂቶ የማስተማር አተገባበራቸውን መመርመር ነው፡፡የጥናቱ ጥያቄዎችም ፡- መምህራን ፣ በመሰረታዊ የቋንቋ ክሂሎች መሰረት ፡- እንዴት አድርገው አቀናጂተው ያስተምራሉ? አቀናጂተው ሲያስተምሩ የሚያጋጥሟቸው እንቅፋቶች ምን ምን ናቸው? የሚሉ ናቸው፡፡ በውጤት ትንተናው መሰረት፣በምልከታ፣በጽሁፍ መጠየቅእና በሰነድ ፍተሻ የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴዎች አማካኝነት የተሰበሰበው መረጃ ግልጽ የሆነ ውጤት ሰጥቷል፡፡ ይህም የመረጃ ውጤት የአማርኛ ቋንቋ መምህራን፡- በማደመጥ ክሂል፣በንግግር ክሂል ፣በማንበብ ክሂል ፣እና በመጻፍ ክሂል ትምህርት ጊዜ፣ሁለት እና ከሁለት በላይ የሚሆኑ የቋንቋ ክሂሎችን አቀናጂተው እንዳሚያስተምሩ አመልክቷል፡፡በትምህርትም ወቅት በርካታ እንቅፋቶች እንደተከሰቱ መረጃው ጠቁሟል፡፡ከእነዚህም ውስጥ፡- መምህራን፣ክሂሎችን እና ሌሎችን የእውቀት ዘርፎች አቀናጂቶ ለማስተማር ሆነ ለመማር የሚያግዝ የትምህርት መርጃመሳሪያ ተጠቅመው አለማስተማር፣ለማስተማር በቂዝግጂት አለማድረግ፣ መሰረታዊ የቋንቋ ክሂሎችንእና የእውቀት ዘርፎችን አቀናጂቶ ለማስተማርም ሆነ ለመማር ሆነ ተብሎታስቦበት የተሰራ ምቹ የሆነ የተማሪ የመቀበጫ ወንበሮችአለመኖር፣የመምህር እጥረት፣የመማሪያ መጽሀፍ እጥረት ፣ አጋዥ የአማርኛ ቋንቋ መጽሀፍ አለመኖር ፣ቤተ መጽሀፍ አለመኖርእናሌሎች መሰልችግሮች እንነበሩ የተገኘው ውጤት ያስረዳል፡፡ en_US
dc.description.sponsorship uog en_US
dc.language.iso other en_US
dc.publisher uog en_US
dc.relation.ispartofseries Report;
dc.subject ይህ ጥናት ገላጭ ስልትን ተከትሎ የተሰራ እና በዓይነቱዓይነታዊ እና መጠናዊ የሆነ ጥናት ነው en_US
dc.title የአስራ አንደኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መምህራን፣ ክሂሎችን አቀናጅቶ የማስተማር አተገባበር ፍተሻ (በነቀምት እና በአንገር ጉትን የመንግስት መሰናዶ ትምህርት ቤት ተተኳሪነት) en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record

Search in the Repository


Advanced Search

Browse

My Account