Abstract:
ይህ ጥናት ገላጭ ስልትን ተከትሎ የተሰራ እና በዓይነቱዓይነታዊ እና መጠናዊ የሆነ ጥናት
ነው፡፡የጥናቱ ተሳታፊዎችም ፡- በምስራቅ ወለጋ ዞን ፣ በነቀምት እና በአንገር ጉትን የመንግስት
የመሰናዶ ትምህርት ቤት ፣ በ2011 ዓ.ም በአስራ አንደኛ የክፍል ደረጃ አማርኛ ቋንቋን
በማስተማር ላይ የሚገኙ በጥቅል የናሙና ዘዴ የተመረጡ 5 መምህራን እንዲሁም በዚሁ
የክፍል ደረጃ የሚማሩ ከ519 ተማሪዎች መካከል በቀላል እድል ሰጭ የናሙና ዘዴ የተመረጡ
130 ተማሪዎች ተጠኝዎች ሁነዋል፡፡በመሆኑም በመምህራን የክፍል ውስጥ ምልከታ ፣
በተማሪዎች የጽሁፍመጠየቅእና በሰነድ ፍተሻ(የአስራ አንደኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ የመምህር
መምሪያ መጽሀፍ) አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች ተሰብስበዋል፡፡የጥናቱ ዋና ዓላማም ፡- የነቀምት
እና የአንገር ጉትን የመንግስት መሰናዶ ትምህርት ቤት፣ የአስራ አንደኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ
መምህራን፣ክሂሎችን አቀናጂቶ የማስተማር አተገባበራቸውን መመርመር ነው፡፡የጥናቱ
ጥያቄዎችም ፡- መምህራን ፣ በመሰረታዊ የቋንቋ ክሂሎች መሰረት ፡- እንዴት አድርገው
አቀናጂተው ያስተምራሉ? አቀናጂተው ሲያስተምሩ የሚያጋጥሟቸው እንቅፋቶች ምን ምን
ናቸው? የሚሉ ናቸው፡፡ በውጤት ትንተናው መሰረት፣በምልከታ፣በጽሁፍ መጠየቅእና በሰነድ
ፍተሻ የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴዎች አማካኝነት የተሰበሰበው መረጃ ግልጽ የሆነ ውጤት
ሰጥቷል፡፡ ይህም የመረጃ ውጤት የአማርኛ ቋንቋ መምህራን፡- በማደመጥ ክሂል፣በንግግር
ክሂል ፣በማንበብ ክሂል ፣እና በመጻፍ ክሂል ትምህርት ጊዜ፣ሁለት እና ከሁለት በላይ የሚሆኑ
የቋንቋ ክሂሎችን አቀናጂተው እንዳሚያስተምሩ አመልክቷል፡፡በትምህርትም ወቅት በርካታ
እንቅፋቶች እንደተከሰቱ መረጃው ጠቁሟል፡፡ከእነዚህም ውስጥ፡- መምህራን፣ክሂሎችን እና
ሌሎችን የእውቀት ዘርፎች አቀናጂቶ ለማስተማር ሆነ ለመማር የሚያግዝ የትምህርት
መርጃመሳሪያ ተጠቅመው አለማስተማር፣ለማስተማር በቂዝግጂት አለማድረግ፣ መሰረታዊ
የቋንቋ ክሂሎችንእና የእውቀት ዘርፎችን አቀናጂቶ ለማስተማርም ሆነ ለመማር ሆነ
ተብሎታስቦበት የተሰራ ምቹ የሆነ የተማሪ የመቀበጫ ወንበሮችአለመኖር፣የመምህር
እጥረት፣የመማሪያ መጽሀፍ እጥረት ፣ አጋዥ የአማርኛ ቋንቋ መጽሀፍ አለመኖር ፣ቤተ
መጽሀፍ አለመኖርእናሌሎች መሰልችግሮች እንነበሩ የተገኘው ውጤት ያስረዳል፡፡