Abstract:
የዚህ ጥናት ዋና አላማ የተማሪዎች የቃላት መማር ብልሃቶች፣የቃላት ችሎታና
የቃላት መማር ተነሳሽነት መካከል ያለውን ተዛማዶ መፈተሽ ነው፡፡ የጥናቱ
ተሳታፊዎች በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በከሚሴ ከተማ የኬሚሴ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ
ትምህርት ቤት አስረኛ ክፍል ኦሮምኛ አፍ ፈት ከሆኑ 364 ተማሪዎች መካከል በእድል
ሰጭ ናሙና ዘዴ የተመረጡ 106 ተማሪዎች ናቸው፡፡የጥናቱ አይነት ተዛምዷዊ ሲሆን
ተማሪዎችን የቃላት ችሎታ ለመፈተሽ ፈተና ተፈትነዋል። የቃላት መማር ብልሃቶች
አጠቃቀምን እና የተማሪዌችን የቃላት መማር ተነሳሽነት ለመፈተሽ የፅሁፍ መጠይቅ
እንዲሞሉ ተደርጓል፡፡ በእነዚህ የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴዎች የተሰጠው መረጃ በፒርሰን
የተዛምዶ መወሰኛ ቀመር ተተንትኗል፡፡በጥናቱ ውጤት መሰረትም በቃላት መማር
ብልሃቶችና በቃላት ችሎታ መካከል ጉልህ የሆነ አሉታዊ ተዛምዶ ታይቷል( r=-0.016
, p < 0.05)፡፡ በተመሳሳይ በቃላት መማር ተነሳሽነትና በቃላት ችሎታ መካከል ጉልህ
ያልሆነ አሉታዊ ተዛምዶ ታይቷል(r=0.137, P )፡፡
እንዲሁም በድህረት መጣኝ ትንተና ስሌት መሰረት የቃላት መማር ብልሃቶች
አጠቃቀም እና የተማሪዎች የቃላት መማር ተነሳሽነት የተማሪዎችን የቃላት ችሎታ
የመተንበይ ድርሻ በስታትስቲክስ እጅግ በጣም ዝቅተኛ ሆኗል፡፡በጥናቱ ውጤት
መሰረትም በተማሪዎች የቃላት መማር ብልሃቶች አጠቃቀም፣በቃላት ችሎታ እና
በቃላት መማር ተነሳሽነት መካከል ተዛምዶ የለም፡፡ ይህ ማለት ደግሞ የተማሪዎች
የቃላት መማር ብልሃት አጠቃቀማቸው እየሰፋ ቢሄድም፣የተማሪዎች የቃላት መማር
ተነሳሽነት ቢኖራቸውም በቃላት ችሎታቸው መሻሻል ላይ ድርሻ ሆነ ሚና እንደሌላቸው
ነው። በተጨማሪም የተማሪዎች የቃላት መማር ብልሃቶች አጠቃቀም ሆነ የቃላት
መማር ተነሳሽነት የተማሪዎችን የቃላት ችሎታ ለማሻሻል ድርሻ የለውም።