mirage

ስነፅሁፍ አማርኛ ትምህርት የድህረ ምረቃ መርሃ-ግብር ማስተማሪያነት መጠቀም ድርሰት የመጻፍ አስተዋጽኦ፣ በ11ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት

DSpace Repository

Show simple item record

dc.contributor.author አስማማው, መንገሻ
dc.date.accessioned 2022-03-22T08:12:58Z
dc.date.available 2022-03-22T08:12:58Z
dc.date.issued 2013-03-13
dc.identifier.uri http://hdl.handle.net/123456789/4771
dc.description.abstract የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ ስነጽሁፍን ለቋንቋ ማስተማሪያነት መጠቀም የተማሪዎችን ድርሰት የመጻፍ ችሎታን ለማሻሻል ያለውን አስተዋጽኦ መፈተሽ ነው፡፡ ዓላማውን ለማሳካትም መጠናዊ ምርምር ላይ የተመሰረተ ከፊል ሙከራዊ የጥናት ንድፍን ተግባራዊ አድርጓል፡፡ በአማራ ክልል፣ በምስራቅ ጎጃም ዞን፣ በሸበል በረንታ ወረዳ፣ በየዕድውኃ 2ኛ ደረጃ መሰናዶ ትምህርትቤት በ2013 ዓ.ም. በ11ኛ ክፍል ከሚማሩ 13 ምድብ ተማሪዎች መካከል በአንድ መምህር የሚማሩ ሁለት ምድብ ተማሪዎች በአመቺ የናሙና ስልት ተመርጠዋል፤ የተመረጡትም ምድቦች አንዱን የሙከራ ሌላኛውን የቁጥጥር ብሎ ለመክፈል ተራ የዕጣ ንሞና ዘዴ ጥቅም ላይ እንዲውል ተደርጓል፡፡ የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያ ፈተና እና ምልከታ ሲሆኑ፤ ፈተናው፣ ቅድመ እና ድህረ ፈተናን ያካተተ ነው፡፡ የቅድመ ፈተናው አላማ ሁለቱ ቡድን ተማሪዎች ከትምህርቱ በፊት ድርሰት የመጻፍ ችሎታቸው ተመጣጣኝ መሆኑን ለመፈተሽ ሲሆን፤ የድህረ ፈተናው አላማ የመጻፍ ክሂልን በስነጽሁፍ የተማሩና ባሁኑ ሰዓት እየተተገበረ ባለው ዘዴ በተማሩት የቁጥጥር ቡድን ማሪዎች ድርሰት የመጻፍ ችሎታቸውን መሻሻል አለመሻሻሉን ለመፈተሽ ነው፡፡ ምልከታው የተከናወነበት ዋነኛ ዓላማ ደግሞ የሙከራ ቡድን ተማሪዎች በስነጽሁፍ ቴክስቶች አማካኝነት ድርሰት የመጻፍ ትምህርታቸውን ባግባቡ እየተማሩ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ነው፡፡ የመማር ማስተማር ሂደቱን በመመዝገብም ከምልከታ የተገኘውን መረጃ ለመሰብሰብ ተችሏል፡፡ የሙከራ እና የቁጥጥር ቡድን በቅድመ እና በድህረ ትምህርት ፈተና የተገኙ የፈተና ውጤቶችን ለማነጻጸር በባዕድ ናሙና ቲ-ቴስት፤ እያንዳንዱ ቡድን በቅድመና በድህረ ፈተና ያስመዘገቡትን ውጤት ለማነጻጸር ደግሞ በጥንድ ናሙና ቲ-ቴስት ቀመር እንዲሰሉ ተደርጓል፡፡ በውጤት ትንተናው መሰረት በሙከራ እና በቁጥጥር ቡድን ተማሪዎች መካከል በቅድመ ትምህርት ድርሰት የመጻፍ ፈተና ውጤቶች ላይ ተመጣጣኝ ውጤት የተመዘገበ ሲሆን፤ በሌላ በኩል ደግሞ በሙከራና በቁጥጥር ቡድን en_US
dc.description.sponsorship uog en_US
dc.language.iso en_US en_US
dc.publisher uog en_US
dc.subject በቁጥጥር ቡድን ተማሪዎች መካከል በቅድመ ትምህርት ድርሰት የመጻፍ ፈተና ውጤቶች ላይ ተመጣጣኝ ውጤት የተመዘገበ ሲሆን፤ በሌላ በኩል ደግሞ በሙከራና በቁጥጥር ቡድን en_US
dc.title ስነፅሁፍ አማርኛ ትምህርት የድህረ ምረቃ መርሃ-ግብር ማስተማሪያነት መጠቀም ድርሰት የመጻፍ አስተዋጽኦ፣ በ11ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record

Search in the Repository


Advanced Search

Browse

My Account