Abstract:
የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ ስነጽሁፍን ለቋንቋ ማስተማሪያነት መጠቀም የተማሪዎችን ድርሰት
የመጻፍ ችሎታን ለማሻሻል ያለውን አስተዋጽኦ መፈተሽ ነው፡፡ ዓላማውን ለማሳካትም መጠናዊ
ምርምር ላይ የተመሰረተ ከፊል ሙከራዊ የጥናት ንድፍን ተግባራዊ አድርጓል፡፡ በአማራ
ክልል፣ በምስራቅ ጎጃም ዞን፣ በሸበል በረንታ ወረዳ፣ በየዕድውኃ 2ኛ ደረጃ መሰናዶ
ትምህርትቤት በ2013 ዓ.ም. በ11ኛ ክፍል ከሚማሩ 13 ምድብ ተማሪዎች መካከል በአንድ
መምህር የሚማሩ ሁለት ምድብ ተማሪዎች በአመቺ የናሙና ስልት ተመርጠዋል፤
የተመረጡትም ምድቦች አንዱን የሙከራ ሌላኛውን የቁጥጥር ብሎ ለመክፈል ተራ የዕጣ
ንሞና ዘዴ ጥቅም ላይ እንዲውል ተደርጓል፡፡ የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያ ፈተና እና ምልከታ
ሲሆኑ፤ ፈተናው፣ ቅድመ እና ድህረ ፈተናን ያካተተ ነው፡፡ የቅድመ ፈተናው አላማ ሁለቱ
ቡድን ተማሪዎች ከትምህርቱ በፊት ድርሰት የመጻፍ ችሎታቸው ተመጣጣኝ መሆኑን
ለመፈተሽ ሲሆን፤ የድህረ ፈተናው አላማ የመጻፍ ክሂልን በስነጽሁፍ የተማሩና ባሁኑ ሰዓት
እየተተገበረ ባለው ዘዴ በተማሩት የቁጥጥር ቡድን ማሪዎች ድርሰት የመጻፍ ችሎታቸውን
መሻሻል አለመሻሻሉን ለመፈተሽ ነው፡፡ ምልከታው የተከናወነበት ዋነኛ ዓላማ ደግሞ የሙከራ
ቡድን ተማሪዎች በስነጽሁፍ ቴክስቶች አማካኝነት ድርሰት የመጻፍ ትምህርታቸውን ባግባቡ
እየተማሩ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ነው፡፡ የመማር ማስተማር ሂደቱን በመመዝገብም
ከምልከታ የተገኘውን መረጃ ለመሰብሰብ ተችሏል፡፡ የሙከራ እና የቁጥጥር ቡድን በቅድመ እና
በድህረ ትምህርት ፈተና የተገኙ የፈተና ውጤቶችን ለማነጻጸር በባዕድ ናሙና ቲ-ቴስት፤
እያንዳንዱ ቡድን በቅድመና በድህረ ፈተና ያስመዘገቡትን ውጤት ለማነጻጸር ደግሞ በጥንድ
ናሙና ቲ-ቴስት ቀመር እንዲሰሉ ተደርጓል፡፡ በውጤት ትንተናው መሰረት በሙከራ እና
በቁጥጥር ቡድን ተማሪዎች መካከል በቅድመ ትምህርት ድርሰት የመጻፍ ፈተና ውጤቶች ላይ
ተመጣጣኝ ውጤት የተመዘገበ ሲሆን፤ በሌላ በኩል ደግሞ በሙከራና በቁጥጥር ቡድን