mirage

ስነፅሁፋዊና ኢ-ስነፅሁፋዊ ስራዎችን ተጠቅሞ የአማርኛ ቋንቋን ማስተማር የአንብቦ መረዳት ችሎታንና የማንበብ ፍላጎትን በማጎልበት ረገድ ያላቸው ሚና፤(በ10ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት)

DSpace Repository

Show simple item record

dc.contributor.author ሁሴን, በአንሻ
dc.date.accessioned 2022-03-03T06:49:51Z
dc.date.available 2022-03-03T06:49:51Z
dc.date.issued 2013-03-22
dc.identifier.uri http://hdl.handle.net/123456789/4675
dc.description.abstract የዚህ ጥናት ዋና አላማ ስነፅሁፋዊ እና ኢ-ስነፅሁፋዊ ስራዎችን ተጠቅሞ አማርኛ ቋንቋን ማስተማር የተማሪዎችን የአንብቦ መረዳት ክሂል በማጎልበትና የንባብ ፍላጎትን በማሻሻል ረገድ ያለውን ሚና መመርመር ነው፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎች በደቡብ ጎንደር ዞን በደራ ወረዳ በአንበሳሜ መሠናዶና አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ከሚገኑት 920 ተማሪዎች መካከል በእድል ሰጭ ናሙና ዘዴ የተመረጡ የሁለት ክፍል ተማሪዎች በድምሩ 80 ተማሪዎች ናቸው፡፡ ከእነርሱም በፈተና እና በፅሁፍ መጠይቅ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች ተሰብስበዋል፡፡ የተሰበሰቡት መረጃዎች ጥንድ ናሙና ቲ-ቴስት ተሰልተው በገላጭና ድምዳሜያዊ ስታስቲክስ ተተንትነዋል፡፡ በዚህም መሰረት በስነ ፅሁፋዊ እና ኢ-ስነፅሁፋዊ ስራዎች ቋንቋን ማስተማር የቅድመ ትምህርት ፈተና አማካይ ውጤት መካከል በስታስቲክስ ጉልህነት ያለው አይደለም፡፡ (t=0.849, df=78, sig=0.825)፡፡ይሁን እንጅ የድህረ ሙከራ ውጤት እንደሚያሳየው በስነፅሁፋዊ ስራዎች አማርኛ ቋንቋን ማስተማር የድህረ ሙከራ በኢ-ስነፅሁፋዊ ስራዎች አማርኛ ቋንቋን ማስተማር የድህረ ሙከራ ውጤት የአማካይ ልዩነት ስታስቲካዊ ጉልህነት እንዳለው ተረጋግጧል (t=9.213, df=78, sig=0.000)፡፡ በሌላ በኩል የሁለቱም ቡድኖች ማለትም ስነፅሁፋዊ ስራዎችን ተጠቅሞ አማርኛ ቋንቋን ማስተማር እና ኢ-ስነፅሁፋዊ ስራዎችን ተጠቅሞ አማርኛ ቋንቋን ማስተማር የቅድመ እና የድህረ ትምህርት ፍላጎት የፅሁፍ መጠይቅ ውጤት መካከል በስታስቲክስ ጉልህ ልዩነት (P<0.05) ታይቷል፡፡ በሌላ መልኩ ኢ-ስነፅሁፋዊ ስራዎችን በመጠቀም የተማሩት ቡድኖች ዳግም በስታስቲክሰ ጉልህ ልዩነት (P>0.05)ሆኗል፡፡ ይህ በጥናቱ ውጤት መሠረትም ስነፅሁፋዊ ስራዎችን ተጠቅሞ የአማርኛ ቋንቋን ማስተማር የተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታና የማንበብ ፍላጎት ለማሳደግ ጠቃሚ መሆበመፍትሔነት ተጠቁሟል፡ en_US
dc.description.sponsorship uog en_US
dc.language.iso other en_US
dc.publisher uog en_US
dc.subject የዚህ ጥናት ዋና አላማ ስነፅሁፋዊ እና ኢ-ስነፅሁፋዊ ስራዎችን ተጠቅሞ አማርኛ ቋንቋን ማስተማር የተማሪዎችን የአንብቦ መረዳት ክሂል በማጎልበትና የንባብ ፍላጎትን በማሻሻል ረገድ ያለውን ሚና መመርመር ነው፡ en_US
dc.title ስነፅሁፋዊና ኢ-ስነፅሁፋዊ ስራዎችን ተጠቅሞ የአማርኛ ቋንቋን ማስተማር የአንብቦ መረዳት ችሎታንና የማንበብ ፍላጎትን በማጎልበት ረገድ ያላቸው ሚና፤(በ10ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት) en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record

Search in the Repository


Advanced Search

Browse

My Account