Abstract:
የዚህ ጥናት ዋና አላማ ስነፅሁፋዊ እና ኢ-ስነፅሁፋዊ ስራዎችን ተጠቅሞ አማርኛ ቋንቋን ማስተማር
የተማሪዎችን የአንብቦ መረዳት ክሂል በማጎልበትና የንባብ ፍላጎትን በማሻሻል ረገድ ያለውን ሚና መመርመር
ነው፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎች በደቡብ ጎንደር ዞን በደራ ወረዳ በአንበሳሜ መሠናዶና አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ
ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ከሚገኑት 920 ተማሪዎች መካከል በእድል ሰጭ ናሙና ዘዴ የተመረጡ
የሁለት ክፍል ተማሪዎች በድምሩ 80 ተማሪዎች ናቸው፡፡ ከእነርሱም በፈተና እና በፅሁፍ መጠይቅ አስፈላጊ
የሆኑ መረጃዎች ተሰብስበዋል፡፡ የተሰበሰቡት መረጃዎች ጥንድ ናሙና ቲ-ቴስት ተሰልተው በገላጭና
ድምዳሜያዊ ስታስቲክስ ተተንትነዋል፡፡ በዚህም መሰረት በስነ ፅሁፋዊ እና ኢ-ስነፅሁፋዊ ስራዎች ቋንቋን
ማስተማር የቅድመ ትምህርት ፈተና አማካይ ውጤት መካከል በስታስቲክስ ጉልህነት ያለው አይደለም፡፡
(t=0.849, df=78, sig=0.825)፡፡ይሁን እንጅ የድህረ ሙከራ ውጤት እንደሚያሳየው በስነፅሁፋዊ ስራዎች አማርኛ ቋንቋን ማስተማር የድህረ
ሙከራ በኢ-ስነፅሁፋዊ ስራዎች አማርኛ ቋንቋን ማስተማር የድህረ ሙከራ ውጤት የአማካይ ልዩነት ስታስቲካዊ
ጉልህነት እንዳለው ተረጋግጧል (t=9.213, df=78, sig=0.000)፡፡ በሌላ በኩል የሁለቱም ቡድኖች ማለትም
ስነፅሁፋዊ ስራዎችን ተጠቅሞ አማርኛ ቋንቋን ማስተማር እና ኢ-ስነፅሁፋዊ ስራዎችን ተጠቅሞ አማርኛ ቋንቋን
ማስተማር የቅድመ እና የድህረ ትምህርት ፍላጎት የፅሁፍ መጠይቅ ውጤት መካከል በስታስቲክስ ጉልህ ልዩነት
(P<0.05) ታይቷል፡፡ በሌላ መልኩ ኢ-ስነፅሁፋዊ ስራዎችን በመጠቀም የተማሩት ቡድኖች ዳግም በስታስቲክሰ
ጉልህ ልዩነት (P>0.05)ሆኗል፡፡ ይህ በጥናቱ ውጤት መሠረትም ስነፅሁፋዊ ስራዎችን ተጠቅሞ የአማርኛ
ቋንቋን ማስተማር የተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታና የማንበብ ፍላጎት ለማሳደግ ጠቃሚ መሆበመፍትሔነት ተጠቁሟል፡