dc.contributor.author | ባይለየኝ, መላኩ | |
dc.date.accessioned | 2022-03-22T08:06:08Z | |
dc.date.available | 2022-03-22T08:06:08Z | |
dc.date.issued | 2013-03-13 | |
dc.identifier.uri | http://hdl.handle.net/123456789/4770 | |
dc.description.abstract | የዚህ ጥናት ዓብይ አላማ ሂደት ተኮር የመፃፍ ት/ት ዓቀራረብ የተማሪዎችን የመፃፍ ችሎታና ተነሣሽነት ለማጐልበት ያለውን ሚና መመርመር ነው፡፡ ጥናቱ ከፊል ፍትነታዊ ሲሆን፣ የተካሄደው በአማራ ክልል በምስራቅ ጐጃም ዞን በሉማሜ ከተማ በሉማሜ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ት/ቤት የዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች ላይ ያተኮረ ነው፡፡ ከዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል በቅድመ ፈተና በተለዩ አንድ የሙከራ ቡድን እና በአንድ የቁጥጥር ቡድን ላይ ተካሂዷል፡፡ የጥናቱ ቦታ በአመቺ የናሙና ስልት የጥናቱ ተተኳሪዎች በዓላማ ተኮር የንሞና ዘዴ ተመርጧል፡፡ የልምምድ ተግባሩን የሚሰጥ አንድ መምህር በአላማ ተኮር ናሙና ዘዴ ተመርጧል የጥናቱ የመረጃ ምንጨች ቅድመና ድህረ ፈተና እንዲሆን ቅድመና ድህረ የፅሁፍ መጠይቅ ናቸው፡፡ ቅድመ ፈተናው የተሰጠበት አላማ ተማሪዎች ከሙከራ ጥናቱ በፊት ያላቸውን የመጻፍ ውጤት ተቀራራቢ መሆን/ አለመሆኑን ለመፈተሸ ሲባል ነው፡፡ የድህረ ፈተናው አላማ ደግሞ የሙከራና የቁጥጥር ቡድን ሆነው የተመረጡት ተማሪዎች በተለያዩ የማስተማሪያ ዘዴዎች የመጻፍ ክሂልን ከተማሩ በኃላ በመካከላቸው ጉልህ ልዩነት መኖር/ አለመኖሩን ለማረጋገጥ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ቅድመ የፅሁፍ መጠይቅ እንዲሞሉ የተደረገበት አላማ ተማሪዎች ከሙከራ ጥናቱ በፊት ያላቸውን የመፃፍ ተነሣሽነት ተቀራራቢ መሆን አለመሆኑን ለመፈተሽ ነው፡፡ ድህረ የፅሁፍ መጠይቅ እንዎች የመፃፍ ክሂልን ከተማሩ በኋላ በመካከላቸው ጉልህ ልዩነት መኖር አለለመኖሩን ለማረጋገጥ ነው፡፡ በቅድመ ፈተናና የፅሁፍ መጠይቅ እንዲሁም በድህረ ፈተናና የፅሁፍ መጠይቅ የተገኘው ውጤት በነፃ ናሙና ቲ -ቴስት እንዲሰላ ተደርጓል፡፡ በተጨማሪም በቅድመና በድህረ ፈተና፣ በቅድመና በድህረ የፅሁፍ መጠይቅ የተገኙ ውጤቶች በጥንድ ናሙና ቲ -ቴስት ቀመር እንዲሰላ ተደርጓል፡፡ | en_US |
dc.description.sponsorship | uog | en_US |
dc.language.iso | en_US | en_US |
dc.publisher | uog | en_US |
dc.subject | በተጨማሪም በቅድመና በድህረ ፈተና፣ በቅድመና በድህረ የፅሁፍ መጠይቅ የተገኙ ውጤቶች በጥንድ ናሙና ቲ -ቴስት ቀመር እንዲሰላ ተደርጓል፡፡ | en_US |
dc.title | ሂደት ተኮር የመፃፍ ትምህርት አቀራርብ የተማሪዎችን የመፃፍ ችሎታና ተነሳሽነት ለማጎልበት ያለው ሚና (በዘጠነኛ ክፍል ተተኳሪነት) | en_US |
dc.type | Thesis | en_US |