Abstract:
የዚህ ጥናት ዓቢይ ዓላማ የተማሪዎች የስብዕና አይነት ከአንብቦ መረዳት ችሎታ ጋር ያለው
ዝምድና ምን እንደሚመስል መመርመር ነበር፡፡ ይህን ለማሳካት በአመቺ የናሙና የአመራረጥ
ስልት ከተመረጠው ከማክሰኝት ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ት/ቤት የአስራ አንደኛ ክፍልን
ከሌሎች ከ9-12 ካሉ ክፍሎች በቀላል የእጣ ናሙና አመራረጥ በ 8 ክፍሎች ተመድበው
ከሚማሩ የ11ኛ ክፍል ተማሪዎችን በቀላል እጣ ናሙና በሁለቱ መማሪያ ክፍሎች የሚማሩትን
ተማሪዎች ግን ሁሉንም በመውሰድ ተፈላጊው መረጃ ተሰብስቧል፡፡ የመረጃ መሰብሰቢያ ስልቶች
ባለ 20 የምርጫ ጥያቄ የአንብቦ መረዳት ፈተናና ባለ 15 የምርጫ ጥያቄ የሰብእና አይነት
መጠየቅ በ5ቱ ዋና ዋና የሰብእና አይነቶች ማለትም በጥንቁቅ፣ ግልጸኝነት፣ ተስማሚ፣
አይናፋር እና ተግባቢ ላይ የተዘጋጀ ነበር፡፡ የተሰበሰበው መረጃ SPSS በተባለ የኮምፒተር
መተግበሪያ ገላጭና ኢንፈረንሺያል ስታትስቲክስ ማለትም አማካኝ፣ የፒርሰን ዝምድናና ህብረ
ድህረታዊ ትንተና ተሰርቷል፡፡ ከውጤት ትንተናው መረዳት እንደተቻለውም በመጀመሪያ
የሰብእና መጠይቁ ተማሪዎችን በ5 የተለያዩ የሰብእና አይነቶች ማለትም በጥንቁቅ፣
ግልጸኝነት፣ ተስማሚ፣ አይናፋር እና ተግባቢ በሚባሉት ላይ ተማሪዎች በመካከለኛ ደረጃ
(አማካይ፣8.178፣ጉልህነት-.001) የሚገኙ መሆኑን ማወቅ ማስቻሉን፤ ሲቀጥል የተማሪዎች
የአንብቦ መረዳት ችሎታ ከአማካይ በላይ (አማካይ 15.4) እንዳለ ካስመዘገቡት የፈተና ውጤት
ማወቅ ተችሏል፡፡ ነገር ግን የተማሪዎች አንብቦ የመረዳት ችሎታ ከአጠቃላይ የስብዕና አይነት
አንጻር ጉልህ ተዛምዶ አለመኖሩን (r=.042፤p<0.5) ማየት ተችሏል፡፡ በተመሳሳይ የሰብእና
አይነት ነጥብ የአንብቦ መረዳት ችሎታን ነጥብ ለመተንበይ ያለው ድርሻ አናሳ (R=.292, R2
=
0.085 →8.5%) መሆኑንም የተገኘው የመረጃ ትንተና አሳይቷል፡፡ ስለዚህ የንባብ ክሂልን
ለማስተማር የሚመረጡ ይዘቶችም ሆነ የማስተማሪያ ስልቶች የተማሪዎችን ሰብእና ሳይሆን
ሌሎች የጎላ ተጽእኖ ያላቸውን ሁኔታዎች ቅድሚያ በመስጠት እንዲካሂዱ ይመከራል፡፡