mirage

ከ2007-2011 ዓ.ም ለአንደኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ በቀረቡ ክልል አቀፍና ሞዴል የአማርኛ ቋንቋ ፈተናዎች ውስጥ የተካተቱ የአንብቦ መረዳት ጥያቄዎች የይዘት ተገቢነትና አቀራረብ ፍተሻ

DSpace Repository

Show simple item record

dc.contributor.author ፈቃዱ, ዘመናይ
dc.date.accessioned 2022-03-01T09:00:24Z
dc.date.available 2022-03-01T09:00:24Z
dc.date.issued 2012-05-16
dc.identifier.uri http://hdl.handle.net/123456789/4671
dc.description.abstract ዚህ ጥናት ዓብይ ዓላማ ለአንደኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ በቀረቡ ክልላዊ እና ሞዴል የአማርኛ ቋንቋ ፈተናዎች ተካተው የሚገኙትን የአንብቦ መረዳት ጥያቄዎችን የይዘት ተገቢነትና አቀራረብ መገምገም ነበር፡፡የጥናቱን ዋና ዓላማ ከግብ ለማድረስ አጥኝዋ በሰነድ ፍተሻ በፈተናዎቹ የተካተቱትን የአንብቦ መረዳት ጥያቄዎች የይዘት ተገቢነት በመርሀትምህርቱ የቀረቡበትን ዚህ ጥናት ዓብይ ዓላማ ለአንደኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ በቀረቡ ክልላዊ እና ሞዴል የአማርኛ ቋንቋ ፈተናዎች ተካተው የሚገኙትን የአንብቦ መረዳት ጥያቄዎችን የይዘት ተገቢነትና አቀራረብ መገምገም ነበር፡፡የጥናቱን ዋና ዓላማ ከግብ ለማድረስ አጥኝዋ በሰነድ ፍተሻ በፈተናዎቹ የተካተቱትን የአንብቦ መረዳት ጥያቄዎች የይዘት ተገቢነት በመርሀትምህርቱ የቀረቡበትን ዚህ ጥናት ዓብይ ዓላማ ለአንደኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ በቀረቡ ክልላዊ እና ሞዴል የአማርኛ ቋንቋ ፈተናዎች ተካተው የሚገኙትን የአንብቦ መረዳት ጥያቄዎችን የይዘት ተገቢነትና አቀራረብ መገምገም ነበር፡፡የጥናቱን ዋና ዓላማ ከግብ ለማድረስ አጥኝዋ በሰነድ ፍተሻ በፈተናዎቹ የተካተቱትን የአንብቦ መረዳት ጥያቄዎች የይዘት ተገቢነት በመርሀትምህርቱ የቀረቡበት የድግግሞሽ መጠን መሰረት በማድረግ ስፒርማን የተዛምዶ ቀመር በመጠቀም የዝምድና መጠናቸው ተሰልቷል፡፡ከ2007-2011 ዓ.ም ያሉ ክልላዊና ሞዴል ፈተናዎችም በዓላማ ተኮርንሞና ተመርጠው በመረጃ ምንጭነት ውለዋል፡፡በድግግሞሽ ቆጠራ፣ በደረጃ፣ በስፒርማን የተዛምዶ ቀመር እና በገለጻ የተተነተኑት መረጃዎች ውጤትም ቀጥሎ ቀርቧል፡፡ የመጀመሪያው ዓላማ ለአንደኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ በተዘጋጁት ክልል አቀፍ የአማርኛ ቋንቋ ፈተናዎች የተካተቱት የአንብቦ መረዳት ጥያቄዎች የይዘት ተገቢነት ከመርሃትምህርቶቹ አንጻር ተገቢነት የጎደላቸው መሆኑ ተስተውሏል፡፡ በመርሃትምህርቶቹና በፈተናዎቹ ጥያቄዎች መካከልም ጉልህ ያልሆነ አዎንታዊ ዝምድና (n=5, r=.671,p>0.05) ተስተውሏል፡፡ሁለተኛውዓላማ ለአንደኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ በተዘጋጁት ሞዴል የአማርኛ ቋንቋ ፈተናዎች የተካተቱት የአንብቦ መረዳት ጥያቄዎች የይዘት ተገቢነት ከመርሃትምህርቶቹ አንጻር ሲታዩ ደግሞ ሞዴል ፈተናዎቹ በበለጠ የይዘት ተገቢነት የጎደላቸው ሆነዋል፡፡ በመርሃትምህርቶቹና በሞዴል ፈተናዎቹ መካከልም ጉልህ ያልሆነ አሉታዊ ዝምድና (n=5, r=-.459, p>0.05) ተስተውሏል፡፡ የሶስተኛው ዓላማ፣ በክልል አቀፍና ሞዴል ፈተናዎች የአንብቦ መረዳት ጥያቄዎች ይዘት ተገቢነት መካከል ክፍተት መኖሩ ተስተውሏል፡፡ ዝምድናቸውም ጉልህ ያልሆነ አሉታዊ (n=5, r=-.616, p>.0.05) ነው፡፡ አራተኛው ዓላማ፣ ለአንደኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ በተዘጋጁት ክልል አቀፍ ፈተናዎች የተካተቱ የአንብቦ መረዳት ጥያቄዎች ከምርጫ ጥያቄዎች አቀራረብ አንጻር፣ የአንብቦ መረዳት ጥያቄዎች አቀራረብ፣ ተመሳሳይ ፍች ያላቸውን ቃላት በአማራጭነት አለማቅረብ፣ ዝርዝር መረጃዎች፣ እውነታዎች መካተት፣ ትክክለኛው መልስ ከምንባቡ መገኘት አለበት ፣አማራጮቹ ከጥያቄዎቹ ጋር ሰዋሰዋዊ ስምሙነት፣ አንድ ጥያቄ አንድ መልስ ብቻ መያዝና ከፍተኛ ማሰብን የሚያበረታቱ የሚሉትን ሙሉ በሙሉ ያሟሉ ሆነዋል፡፡ በአንጻሩ አራት ጥያቄዎች መሪው በጥያቄያዊ/ክፍት ቦታ ቅርጽ መቅረብ ያልቻለ፣ስድስት ጥያቄዎች ቴክኒካል በሆነ መልክና ያለምንባብ ሊመለሱ የሚችሉ መሆናቸው፣ በፈተናዎቹ የጸሃፊውን አመለካከት መጠየቅ አለመካተት በድክመት የሚጠቀሱ ሆነዋል፡፡ በመጨረሻም የሞዴል ፈተናዎች ከምርጫ ጥያቄዎች አቀራረብ አንጻር ሲታዩ አራት ጥያቄዎች መሪ ጥያቄያቸው በጥያቄ ወይም በክፍት ቦታ መልክ ያልቀረቡ፣ 11 ጥያቄዎች ቴክኒካል በሆነ መልክና ያለምንባብ ሊመለሱ የሚችሉ መሆናቸው፣ አራት ጥያቄዎች አማራጮቹ ከጥያቄዎቹ ጋር ሰዋስዋዊ ስምሙነት የሌላቸው መሆኑ፣ የጸሃፊውን አመለካከት የሚጠይቁ ጥያቄዎች ጭራሽ አለመካተት፣ አጠቃላይ የሞዴል ጥያቄዎቹ ብዛት ከክልላዊ ፈተናዎች እኩል መጠን (77) መሆን ሲገባው42 ብቻ መሆኑ በድክመት የሚታይ ነው፡፡ በአንጻሩ ከቀረቡት ጥያቄዎች፣ አራቱ ከፍተኛ ማሰብን የሚጠይቁ መሆናቸው፣ እያንዳንዱ ጥያቄ አንድ መልስ ብቻ መያዙ እና በአብዛኛው የቀረቡትን መስፈርቶች ማሟላታቸው በጥንካሬ ይጠቀሳል፡፡ ከዚህ በመነሳትም አጥኝዋ ሁለቱም ፈተናዎች ከችግር ነጻ ሆነው ለተማሪዎች መቅረብ ሲገባቸው በርካታ ችግሮች ያሏቸው በመሆኑ አዘጋጆቹ ተገቢ ክትትል፣ድጋፍና ስልጠና ቢያገኙ መልካም ነው፤ የሚል መፍትሄ ጠቁማለች፡፡ en_US
dc.description.sponsorship uog en_US
dc.language.iso other en_US
dc.publisher uog en_US
dc.relation.ispartofseries Report;
dc.subject ዓብይ ዓላማ ለአንደኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ በቀረቡ ክልላዊ እና ሞዴል የአማርኛ ቋንቋ ፈተናዎች ተካተው en_US
dc.title ከ2007-2011 ዓ.ም ለአንደኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ በቀረቡ ክልል አቀፍና ሞዴል የአማርኛ ቋንቋ ፈተናዎች ውስጥ የተካተቱ የአንብቦ መረዳት ጥያቄዎች የይዘት ተገቢነትና አቀራረብ ፍተሻ en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record

Search in the Repository


Advanced Search

Browse

My Account