mirage

የአማርኛ ቋንቋ መምህራን በተማሪዎቻቸው የድርሰት ጽሁፍ መልመጃ ላይ የሚሰጡት ጽሁፋዊና ቃላዊ እርማት ትንተና በ

DSpace Repository

Show simple item record

dc.contributor.author መልካ, የሺ
dc.date.accessioned 2021-02-23T08:34:53Z
dc.date.available 2021-02-23T08:34:53Z
dc.date.issued 2012-08-26
dc.identifier.uri http://hdl.handle.net/123456789/3324
dc.description.abstract የጥናቱ ዋና አላማ መምህራን በድርሰት መልመጃዎች ላይ የሚሰጡትን የጽሁፍና የቃል እርማት መተንተን ነው። ጥናቱ ገምጋሚ የአጠናን ንድፍን የተከተለ ሲሆን አይነታዊ የአጠናን ዘዴ ተግባር ላይ ውሏል፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎች በጨና፣ ቁልሽና ሽሽንዳ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2012 ዓ.ም ዘጠነኛ ክፍል አማርኛ ቋንቋ በማስተማር ላይ ያሉ አራት መምህራን በጠቅላይ የንሞና ዘዴ ተመርጠዋል። ጥናቱን ከግብ ለማድረስ በመረጃነት ያገለገሉት በመምህራን የጽሁፍ እርማት የተሰጠባቸው ድርሰቶች፣ በመቅረጸምሥል ከተቀረጹ ምልከታዎች የተገኙ የቃል እርማቶችና ቃለመጠይቅ ናቸው። መምህራን የሰጧቸው የጽሁፍና የቃል እርማቶች ከእርማት አይነቶች፣ የእርማት አሰጣጥ ስልቶችና ባህርያት አንጻር በአይነታዊ ዘዴ ተተንትነዋል። በመረጃ ትንተናው መሰረትም መምህራን ትዕዛዛዊ የእርማት አይነትን አዘውትረው እንደሚጠቀሙ፣ መርጦ የማረም ስልትንና አሉታዊ የእርማት አሰጣጥ ባህርያትን በብዛት ተጠቅመው በተማሪዎች ጽሁፍ ላይ እርማት እንደሚሰጡ የጥናቱ ውጤት አመልክቷል። ስለሆነም መምህራን ተመሳሳይ የሆነ የእርማት አሰጣጥ ሂደት አዘውትረው ከሚጠቀሙ ይልቅ እንደአስፈላጊነቱ የተለያዩ የእርማት አሰጣጥ ሂደቶችን በማጣመር ተግባራዊ ቢያደርጉ የሚል አስተያየት ቀርቧል፡፡ የወደፊት የጥናቶች ትኩረትም የተለያዩ የእርማት አሰጣጥ ሂደቶች ከመጻፍ ክሂል በተጨማሪ በሌሎች ክሂሎች (በመናገር፣ በማንበብና በማዳመጥ) ላይ የሚኖራቸውን አስተዋጽኦ በስፋትና በጥልቀት መመርመር አስፈላጊ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡ en_US
dc.description.sponsorship uog en_US
dc.language.iso other en_US
dc.publisher uog en_US
dc.relation.ispartofseries report;
dc.subject ወደፊት የጥናቶች ትኩረትም የተለያዩ የእርማት አሰጣጥ ሂደቶች ከመጻፍ ክሂል በተጨማሪ በሌሎች ክሂሎች (በመናገር፣ በማንበብና በማዳመጥ) ላይ የሚኖራቸውን አስተዋጽኦ በስፋትና በጥልቀት መመርመር አስፈላጊ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡ en_US
dc.title የአማርኛ ቋንቋ መምህራን በተማሪዎቻቸው የድርሰት ጽሁፍ መልመጃ ላይ የሚሰጡት ጽሁፋዊና ቃላዊ እርማት ትንተና በ en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record

Search in the Repository


Advanced Search

Browse

My Account