Abstract:
የጥናቱ ዋና ዓላማ በጉሃላ ኣጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ10ኛ ክፍል የሴትና
የወንድ ተማሪዎች አዳምጦ የመረዳት ችሎታ ምን እንደሚመስል መፈተሽ ነው። የጥናቱ
ተሳታፊዎች በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በምስራቅ በለሳ ወረዳ በጉሀላ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
በ2012 ዓም የሚማሩ የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች ናቸው። በጥናቱ በአስር የመማሪያ ክፍሎች
የሚማሩ 50 ተማሪዎች በዕድል ሰጭ የንሞና ዘዴ በናሙናነት ተመርጠዋል። ከእነሱም
አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች በአዳምጦ የመረዳት ችሎታ ፈተና ተሰብስቧል። የተሰበሰቡት
መረጃዎች በድምር፣ በአማካይ፣ በመደበኛ ልይይት እና በነጠላ ናሙና ትቴስት ተተንትነው
ተብራርተዋል። በትንተናው መሰረት የተማሪዎች አዳምጦ የመረዳት ችሎታ አማካይ ውጤት
74.4 በመሆኑ የተማሪዎች አዳምጦ የመረዳት ችሎታ ጥሩ መሆኑን እና በሁለቱ ጾታዎች
መካከል ያለው ልዩነት የጎላለ መሆኑ ታይቷል። እንዲሁም ጥናቱ የተማሪዎች አዳምጦ
የመረዳት ችሎታ ውጤት በቂ መሆኑን ቢያሳይም ከዚህ የበለጠ አዳምጦ የመረዳት ችሎታን
እንዲያዳብሩ የተማሪዎችን የማዳመጥ ችሎታ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊፈጥሩ የሚችሉ ነገሮችን
ለመለየትና መፍትሔ ለመስጠት በጥናት ቢዳስሱ።