dc.contributor.author |
ታደሰ, ደረሰ |
|
dc.date.accessioned |
2021-02-23T08:09:33Z |
|
dc.date.available |
2021-02-23T08:09:33Z |
|
dc.date.issued |
2012-09-12 |
|
dc.identifier.uri |
http://hdl.handle.net/123456789/3318 |
|
dc.description.abstract |
የዚህ ጥናት ዋና አላማ በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት መማሪያነት በተዘጋጁት የ9ኛ እና 10ኛ
ክፍሎች በመማሪያ መጽሐፍት ውስጥ የመጻፍ ክሂልን ለማስተማር የቀረቡ መልመጃዎችን
የይዘት አቀራረብ መፈተሸ ነው። ምርምሩ የሰነድ ፍተሻን የመረጃ መሰብሰቢያ በማድረግ
መረጃዎች ተሰብስበዋል፡፡ አይነታዊ የትንተና ዘዴን በመጠቀምም ተተንትኗል ፡፡ በዚህም
መሰረት የተገኘው ውጤት እንደሚያሳየው በሁለቱም ክፍሎች የአማርኛን ጽህፈት ለማስተማር
የቀረቡት መልመጃዎች ይዘት የተፈተሹ ሲሆን እነሱም ቃላትን አገባባዊ ፍቺ የሚያሳዩ
አረፍተነገሮችን መመስረት፣አንቀጽ መጻፍ፣ስርአተነጥቦችን በተገቢው ቦታ ማስገባት፣አያያዥ
ቃላትን መጠቀም፣መንስኤና ውጤት መለየት፣ደብዳቤ መጻፍ እና አስተዋጽኦ መንደፍ
የመሳሰሉትን ይዘቶች ይዟል፡፡ እነዚህን ይዘቶች እንዴት እንደሚጽፉ እና የተገበቡ ወይም
በመጽሀፍ ውስጥ ብቻ የተካተቱትን ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ብቻ ትኩረት በማድረግ መጽሐፍ
የተማሪዎችን ልምድና ማህበራዊ አካባቢ ያላገናዘበ ነው፡፡ምክንያቱም የመጽሀፍ ክሂል ብዙ
ተግባራትን የሚይዝ ነው፤ተማሪዎችን በርዕስ መምረጥ፣አረፍተነገር እንዲያዋቅሩ፣ሃሳብ
ማመንጨት ማደራጀትን ብሎም የአንቀጽ አመሰራረትን ብሎም ድርሰት መጻፍን ችሎታ
የሚጠይቅ ስለሆነ እነዚህን እየጻፉ እንዲማሩ የሚያስችሉ መልመጃዎችን መያዝ
ይኖርበታል፡፡መማሪያ መጽሐፍ ላይ የሚገኙትን የጽሑፍ ክሂል ማዳበሪያ መልመጃዎችን
ዘወትር እንዲጽፉ ማድረግ፡፡ ብሎም በቂ ጊዜ የቋንቋውን ክሂል ለማሳደግ የሚረዱ ስልቶችን
በሥርዓተ ትምህርቱ ውስጥ ትኩረት በመስጠት የሚሻሻልበትን መንገድ መፈለግን
ቀርቧል፡፡ እነዚህም ተማሪዎቹ የዕለት ገጠመኞቻቸውን ፣ህልሞቻቸውን. አሳዛኝና አስደሳች
ጊዜያቸውን እንዲሁም የቀን ውሎ የመጻፍ ክሂል እንዲያዳብሩ ማድረግ የሚሉት ናቸው፡፡
ስለዐረፍተነገር፣ አንቀጽና ድርሰት በሚማሩበት ጊዜ ከንድፈሀሳብ የዘለለ ተግባራዊ ልምምድ
ላይ የተመሠረተ ትምህርት መስጠት እና ጽሕፈትን እንደፈተና ሳይሆን እየተዝናኑ
እንዲያዳብሩት መደገፍ ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የመማሪያ መጽሐፎችን ማራኪና ለመፃፍ
የሚያነሳሱ የተለያዩ ገጠመኞችን እንዳይዝ ማድረግ ተማሪዎች በፍላጎት እና በመነሳሳት
እንዲጽፉ ያደርጋል፡፡ ተማሪዎችን የጽሁፍ ክሂሉ እንዲያዳብሩ ማህበረሰባዊ
አከባቢያቸውን፣ልምዳቸውን ፣ባህላቸውን እና የአለምን ሁለንተናዊ ገጽታ የሚያመላክት
ግንዛቤያቸውን በሚያሳድግ መልኩ የመማሪያ መጽሀፉ ቢዘጋጅ የተሻለ የቋንቋውን ትምህርት
ዓላማ ያሳካል፡፡ የመማሪያ መጽሃፎቹ በተሻለ የማስተማሪያ ዘዴ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች
ቢዘጋጅ የቋንቋን ትምህርት አላማ ከግብ ለማድረስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡ |
en_US |
dc.description.sponsorship |
uog |
en_US |
dc.language.iso |
other |
en_US |
dc.publisher |
uog |
en_US |
dc.relation.ispartofseries |
report; |
|
dc.subject |
አይነታዊ የትንተና ዘዴን በመጠቀምም ተተንትኗል |
en_US |
dc.title |
በ9ኛና በ10ኛ ክፍል የአማርኛ መማሪያ መጽሃፍ ውስጥ የጽህፈት ክሂል ትምህርት ይዘቶቸ አቀራረብ ፍተሻ |
en_US |
dc.type |
Thesis |
en_US |