mirage

ከ2009-2011 ዓ.ም ለአስረኛ ክፍል ተማሪዎች የቀረቡ የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሞዴል ፈተናዎች የይዘት ተገቢነት ፍተሻ

DSpace Repository

Show simple item record

dc.contributor.author በቃሉ, ልዑል
dc.date.accessioned 2021-02-23T07:38:25Z
dc.date.available 2021-02-23T07:38:25Z
dc.date.issued 2012-06-05
dc.identifier.uri http://hdl.handle.net/123456789/3306
dc.description.abstract የዚህ ጥናት አብይ ዓላማ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በልደታ ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅህፈት ቤትከ2009 ዓ.ም እስከ 2011 ዓ.ም ተዘጋጅተው ለአስረኛ ክፍል ተማሪዎች የቀረቡ የአማርኛ ቋንቋትምህርት ሞዴል ፈተናዎች የይዘት ተገቢነት ፍተሻ ላይ ያተኮረ ነበር፡፡ የጥናቱን ዋና አላማ ከግብለማድረስ አጥኝው ገላጭ ንድፍን የተጠቀመ ሲሆን መረጃ የሰበሰበው ደግሞ በሰነድ ፍተሻ አማካኝነትነው፡፡ ጥናቱ የተካሄደበት ክፍለ ከተማ በአመቺ የናሙና አመራረጥ ስልት የተመረጠ ሲሆን የክፍልደረጃው በዓላማ ተኮር የናሙና አመራረጥ ስልትና ሞዴል ፈተናዎቹ ደግሞ በጠቅላይ የናሙናአመራረጥ ስልት አማካኝነት ተመርጠው ለጥናቱ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች በሰነድ ፍተሻ አማካኝነትከተሰበሰቡ በኋላ መጠናዊ በአይነታዊ በተደገፈ ቅይጥ የመረጃ መተንተኛ ስልት አማካኝነት ትንተናው ተካሂዷል፡፡ የጥናቱ ግኝትም በሶስቱ ተከታታይ ዓመታት ሞዴል ፈተናዎች የተካተቱ ይዘቶች ከቋንቋትምህርት ክሂላት ውስጥ መናገርን፣ ማንባብንና መፃፍን እንዲሁም፣ ሁለቱን የእውቀት ዘርፎችማለትም ሰዋስውንና ስነፅሁፍን የተመለከቱ ናቸው፡፡ የማዳመጥን ክሂል የተመለከተ አንድም ጥያቄቦሶስቱ ተከታታይ ዓመታት ሞዴል ፈተናዎች ውስጥ አልተካተተም፡፡ በመሆኑም የቋንቋ ትምህርትንዑሳን ይዘቶች ተገቢ ውክልና እንዳላገኙ ማወቅ ተችሏል፡፡ የሶስቱ ተከታታይ ዓመታት ሞዴልፈተናዎች በተናጠል ከሁለተኛ ደረጃ የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መፃህፍቱ ጋር ያላቸው የዝምድና መጠንበፒርሰን ፕሮዳክት ሞመንት የተዛምዶ መለኪያ ተሰልቶ አዎንታዊና በጣም ከፍተኛ ሲሆን የ201ዓ.ም ሞዴል ፈተና በ(r=0.925, p=0.008) ቀዳሚውን ቦታ ይዟል፡፡ የ2010 ዓ.ም. ሞዴል ፈተና(r=0.915, p=0.010) እና 2009 ዓ.ም. ሞዴል ፈተና (r=0.859, p=0.028) ደግሞ በቅደም ተከተልሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃ ላይ እንደተቀመጡ ጥናቱ አረጋግጧል፡፡ የሶስቱ ተከታታይ ዓመታት ሞዴልፈተናዎች በጥቅል ከመማሪያ መፃህፍቱ ይዘቶች ጋር ያላቸው የዝምድና መጠንም በፒርሰን ፕሮዳክትሞመንት የተዛምዶ መለኪያ ተሰልቶ በአዎንታዊ አቅጣጫ (r=0.909, p=0.012) የግንኙነት መጠንበጣም ከፍተኛ የሚባልና በስታትስቲክስ ትንተና የስህተት ይሁንታ መጠን (p<0.05) ሆኗል፡፡ ሞዴልፈተናዎች ከችሎታ መለኪያ ፈተና አንፃር ሲታዩ ደግሞ በ2010 ዓ.ም የተዘጋጀው የአማርኛ ቋንቋፈተና ሙሉ ለሙሉ የችሎታ መለኪያ ፈተና ሲሆን፣ በአንፃሩ የ2009 እና የ2011 ዓ.ም ሞዴልፈተናዎች ይዘት ከዘጠነኛ እና ከአስረኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መፃህፍት ዝርዝር ይዘቶች እናከትምህርቱ ዓላማዎች ጋር ሙሉ ለሙሉ ቀጥተኛ ዝምድና የሌላቸው በመሆናቸው ሁሉም የችሎታ መለኪያ ፈተናዎች ናቸው ብሎ መደምደም እንደማይቻል የጥናቱ ውጤት አመላክቷል፡፡ በጥናቱ ግኝትላይ በመመስረት የመፍትሄ ሃሳቦች የተጠቆሙ ሲሆን መምህራን የሞዴል ፈተና በሚያዘጋጁበት ጊዜየችሎታ መለኪያ ፈተናን ታሳቢ እያደረጉ ቢያዘጋጁ፣ የፈተና ጉዳይ የሚመለከታቸው አካላትምመምህራን በሚያዘጋጇቸው የሞዴል ፈተና ጥያቄዎች ውስጥ ምን ምን ይዘቶች እንደተካተቱናከመማሪያ መፃህፍቱ ጋር ያላቸው የይዘት ዝምድና ምን እንደሚመስል በመፈተሽ አላስፈላጊ ጥያቄዎችእንዳይካተቱ የማድረግና ለአዘጋጅ መማህራኑም ስለሞዴል ፈተና አዘገጃጀት በየጊዜው ስልጠናዎችንእያዘጋጁ የሚሰጡበት ሁኔታ ቢመቻች የሚል አስተያየት ተጠቁሟል፡፡ en_US
dc.description.sponsorship uog en_US
dc.language.iso other en_US
dc.publisher uog en_US
dc.relation.ispartofseries report;
dc.subject የሶስቱ ተከታታይ ዓመታት ሞዴል ፈተናዎች በጥቅል ከመማሪያ መፃህፍቱ ይዘቶች ጋር ያላቸው የዝምድና መጠንም በፒርሰን ፕሮዳክት ሞመንት የተዛምዶ መለኪያ ተሰልቶ በአዎንታዊ አቅጣጫ (r=0.909, p=0.012) የግንኙነት መጠን በጣም ከፍተኛ የሚባልና በስታትስቲክስ ትንተና የስህተት ይሁንታ መጠን (p<0.05) ሆኗል en_US
dc.title ከ2009-2011 ዓ.ም ለአስረኛ ክፍል ተማሪዎች የቀረቡ የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሞዴል ፈተናዎች የይዘት ተገቢነት ፍተሻ en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record

Search in the Repository


Advanced Search

Browse

My Account