dc.contributor.author |
ጠናጋሻው, ፍቅሬ |
|
dc.date.accessioned |
2021-02-23T07:02:14Z |
|
dc.date.available |
2021-02-23T07:02:14Z |
|
dc.date.issued |
2012-08-21 |
|
dc.identifier.uri |
http://hdl.handle.net/123456789/3297 |
|
dc.description.abstract |
የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ በ2004 ዓመተ ምህረት በትምህርት ሚኒስቴር ተዘጋጅቶ እስከአሁን ድረስ
አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኘውን የ11ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መጽሐፍ የንባብ ክሂልን
ለማስተማር የቀረቡትን ምንባቦች ይዘት አቀራረብና አደረጃጀት በመመርመር መፈተሸ ነው፤ ይህንን
ዓላማ ለማሳካት የተመረጠው ገላጭ የምርምር ንድፍ ሲሆን የተገኙት መረጃዎች ተሰብስበው
በዓይነታዊ የምርምር ዘዴዎች ተተንትነዋል፡፡ጥናቱ የሀገር ውስጥና የውጪ ቀደምት ባለሞያዎችን
ሥራ ላይ መጠነኛ ዳሰሳ አድርጓል፡፡ በተጨማሪም የ11ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መጽሐፍ
ውስጥ የተካተቱት 10 ምንባቦችና 149 መልመጃዎች (ጥያቄዎች) በዋናነት በሠነድ ፍተሻው
ተቃኝተዋል፡፡ጥናቱ በመፅሐፉ ውስጥ የተካተቱት ምንባቦችይዘት አደረጃጀት ከቀላል ወደ ከባድ የተደራጀ
ሲሆን በምክንያታዊነቱ የተደራጀና በመማር ማስተማሩ ሂደት የሚፈጠሩ ችግሮችን ለመቅረፍ ስነጽሁፋዊ
ይዘቱ መስመራዊ/ቀጥተኛ ግንኙነትን በመከተል የተደራጀ መሆኑን አሳይቷል፡፡ ስለሆነም
በመማሪያ መፅሐፉ የተካተቱት ምንባቦች ይዘት የተማሪዎቹን ስነልቦና፣ማህበራዊ ዳራና ስሜት ባገናዘበ
መልኩ የቋንቋ ክሂሎችን ባለ ጊዜና ቁሳቁስ ለማስተማር የሚያስችሉ፣ሳቢና ማራኪ ሆነው መዘጋጀት
እንዳለባቸው የመፍትሔ ሀሳቦችን ይጠቁማል፡፡ የተገኘው የጥናቱ ውጤት የሚያሳየው በመማሪያ
መፅሐፉ ውስጥ የተካተቱት ምንባቦች የተማሪዎች ስነልቦናና፣ የህብረተሰቡን ባህል መሰረት አድርገው
በማዘጋጀት ተማሪዎቹ የራሳቸውን አቅም በመጠቀም የቋንቋ ዕውቀትን፣አመለካከትንና ክህሎትን
ማሳደግ የሚያስችሉ ሆነው ቀርበዋል፡፡ጥናቱ የምንባቦቹን አቀራረብና አደረጃጀት ለመፈተሸ ከዓላማ
አንፃር፣ ከይዘቱ አንፃር፣ የመማር ማስተማር ሥነ-ዘዴና የጥያቄ አሰጣጥን አስመልክቶ፣ በመፅሐፉ
የተካተቱት ስዕላዊ መግለጫዎቹን በተመለከተ የአቀማመጥ ቅደም ተከተሎቹን፣ የአፃፃፍና የቋንቋ
አጠቃቀሙን አስመልክቶ፣ አጠቃላይ የመጽሐፉን ሁኔታ በተመለከተና በመጨረሻም አጠቃላይ
መስፈርቱን በመዘርዘር መገምገሚያ መስፈርት አድርጎ ተጠቅሞበታል፡፡በመጽሐፉ የተካተቱት
ምንባቦችን በትንታኔው መረጃ መሠረት በመፈተሸ የተገኘውን ውጤት አመላክቶ ለማስተማሪያ
የሚቀርበው መጽሐፍ ምን ይዘት ሊኖረው እንደሚገባው የመፍትሔ ሀሳቦችን ለመጠቋቆም ሞክሯል፡፡ |
en_US |
dc.description.sponsorship |
uog |
en_US |
dc.language.iso |
other |
en_US |
dc.publisher |
uog |
en_US |
dc.relation.ispartofseries |
report; |
|
dc.subject |
በተጨማሪም የ11ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መጽሐፍ ውስጥ የተካተቱት 10 ምንባቦችና 149 መልመጃዎች (ጥያቄዎች) በዋናነት በሠነድ ፍተሻው ተቃኝተዋል፡፡ |
en_US |
dc.title |
በ11ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መፅሐፍ ውስጥ የተካተቱት የንባብ ክሂልንለማስተማር የቀረቡ ምንባቦች ይዘት አቀራረብና አደረጃጀት ፍተሻ |
en_US |
dc.type |
Thesis |
en_US |