Abstract:
የዚህ ጥናት ዓቢይ አላማ በጯሂት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመምህራን የሚሰጡ አስተካካይ
ምጋቤ ምላሾች የተማሪዎችን ድርሰት የመጻፍ ችሎታ በማሻሻል ረገድ ያላቸውን ሚና በአስራ አንደኛ
ክፍል ተተኳሪነት መመርመር የሚል ሲሆን በዚህ ስር የተካተቱት ንዑሳን ዓላማዎች ደግሞ
በመምህራን የሚሰጥ አስተካካይ ምጋቤ ምላሽ ድርሰት የመጻፍ ችሎታን የሚያሳድጉ መሆን
አለመሆናቸውን መመርመርና ተማሪዎች በመምህራን በሚሰጣቸው ምጋቤምላሽ ዙረያ ያላቸው
አጠቃላይ አስተያየት መፈተሽ፤የሚሉት ናቸው፡፡ ይህን ዓላማ ለማሳካት ጥናቱ መጠናዊ ምርምር
የተከተለ ነው፡፡ ባለ ሁለት ቡድን ከፊል ፍትነታዊ የምርምር ንድፍን የተከተለ ነው፡፡ የጥናቱ ተሳታፊ
ተማሪዎችም በጯሂት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከሚማሩ ተማሪዎች መካከል ለጥናቱ የተመረጡት
የአስራ አንደኛ ክፍል ተማሪዎችን ነው፡፡ ከሌሎቹ የክፍል ደረጃዎች ይልቅ 11ኛ ክፍል በዓላማ ተኮር
ናሙና የተመረጠ ሲሆን የክፍሉ ተማሪዎች በአካታች ናሙና በጥናቱ ተሳትፈዋል፡፡ እነዚህ ተማሪዎች
በሙከራና በቁጥጥር ቡድን በመክፈል በሙከራ ቡድን ሃያ አንድ ተማሪዎች አስተካካይ የፅሁፍ ምጋቤ
ምለሽ በመስጠትና ለቀሪዎቹ ሃያ አንድ ተማሪዎች ደግሞ በቁጥጥር ቡድን ምንም ዓይነት አስተካካይ
የፅሁፍ ምጋቤ ምለሽ ባለመስጠት ለለአምሰት ሳምንት በቀን ለሁለት ሰዓት ድርሰት በመፃፍ
እንዲለማመዱ ተደርጓል፡፡ ለጥናቱ መረጃ የተሰበሰበበት መሳሪያ የቅድመና የድህረ የድርሰት ልምምድ
ፈተናዎች ናቸው፡፡ በፈተና የተገኙት መረጃዎች በጥንድ ናሙና ቲ-ቴስት (Paired Samples t-test)
የስሌት ቀመር አማካኝነት ተሰልተው የተገኘውን ውጤት ተተንትኖ ቀርቧል፡፡ በመረጃ ትንተናው
መሰረት በሙከራና በቁጥጥር ቡድኖች በቅድመና በድህረ ፈተና ውጤት መካከል የጎላ ልዩነት ተገኝቷል
P<0.001 ፡፡ አስተካካይ ምጋቤ ምላሽ የተሰጣቸው ተማሪዎች ከሌላው ቡድን ይልቅ በጉልህ ደረጃ
ከፍተኛ አማካይ ውጤት አስመዝግበዋል፡፡ በተመሳሳይ በእያንዱ ቡድን የቅድመና የድህረ ልምምድ
ፈተና ውጤት መካከል የአማካይ ውጤት ልዩነት ጉልህ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በመሆኑም በአስተካካይ
የፅሁፍ ምጋቤ ምላሽ መስጫ ዘዴዎች ምጋቤ ምላሽ የተሰጣቸው ተማሪዎች ድርሰት የመፃች ችሎታ
መሻሻል አሳይቷል፡፡ በመሆኑም የአማርኛ ቋንቋ መምህራን አስተካካይ ምጋቤ ምላሽ በመጠቀም
ድርሰት መፃፍን ቢያስተምሩ የተማሪዎች ድርሰት የመፃፍ ችሎታ ይሻሻላል፡፡