dc.contributor.author | ሺባባው ሞላ1, አራጋው | |
dc.date.accessioned | 2019-01-10T07:25:15Z | |
dc.date.available | 2019-01-10T07:25:15Z | |
dc.date.issued | 2018-07-05 | |
dc.identifier.uri | http://hdl.handle.net/123456789/1904 | |
dc.description.abstract | ይህ ጥናት በሶስተኛና በአራተኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መጻህፍት የስርዓተጾታ ፍትሃዊነት ምን እንደሚመስሉ መመርመር ላይ ያተኮረ ነው። ለዚህም ሁለቱ መማሪያ መጻህፍት በዓላማ ተኮር ስልት ተመርጠዋል። መረጃዎችም በሰነድ ፍተሻ ስልት ተሰብስበዋል። የተሰበሰቡ መረጃዎም በካይ ካሬ፣ በድግግሞሽ ቆጠራ፣በሬሾና በመቶኛ ተተንትነዋል። ከተገኘው ትንተና እንደተስተዋለውም፣ ሴቶች በስም የቀረቡበት የድግግሞሽ መጠን 66(54.09%) ሲሆን ወንዶች የቀረቡበት የድግግሞሽ መጠን ደግሞ 56(45.9%) ነው። የካይ ካሬ ፍተሻ እንዳሳየውም p>0.05 ሆኗል። የጉልህነት ውጤቱም .157 ሆኗል። ይህም በሁለቱ ጾታዎች መካከል የጎላ ልዩነት እንደሌለ የሚያሳይ ነው። የሴት ወንድ የስም ድግግሞሽ ሬሾ/ጥምርታ/ ሲታይ ደግሞ 1.12 ሴት ለ1 ወንድ ነው፡፡ ከዚህ አንጻርም በጾታ ድግግሞሽ የጎላ ልዩነት አልተስተዋለበትም። የሁለቱ ጾታዎች ማህበራዊ ሚና ሲታይ መጻህፍቱ ሴቶች ዋናዋና በሚባል ደረጃ በብዛት የቀረቡበት ሚና የለም። ከተሳተፉባቸው ሚናዎች መካከል ግን ሴቶችን መግረዝ፣ ዳቦ መግዛት፣ ዳቦ መሸጥ፣ ልጅ መንከባከብ፣ የህክምና ምክር መስጠት፣ መብት መጠየቅ፣ በሽተኛ መንከባከብ ይገኙበታል። ኳስ መጫዎት፣ በሽተኛ ተሸካሚ መሆን፣ ሩጫ ደጋፊ መሆን፣ ሳርቤት መክደን፣ፖሊስና ሹፌር ሆኖ መስራት ወንዶች በብዛት የተሳተፉባቸው ዋናዋና ሚናዎች ናቸው። ከዚህ አንጻር ሚና ላይ የፍትሃዊነት ችግር አለ ማለት ይቻላል፡፡ ውክልናን በተመለከተ ደግሞ በሁለቱም ጾታዎች ሴት ወይም ወንድ ሲባል ትዝ በሚል መንገድ የተስተዋሉ ውክልናዎች የሉም ማለት ይቻላል፡፡ ሳይደጋገሙ የቀረቡ ውክልናዎች ሲታዩ ግን ወንዶች በአንጻራዊነት በተሻሉ ነገሮች የተወከሉ ሲሆን ሴቶች ደግሞ ዝቅ ባሉ ነገሮች ተወክለው ቀርበዋል። ይህም ከውክልና አንጻር ክፍተት መኖሩን የሚያሳይ ነው። በመሆኑም ወደፊት የስርዓተትምህርት አዘጋጆች በሚያዘጋጇቸው መጻህፍት ጥንካሬዎቹን በማስቀጠል በድክመቶቹ በኩል ማሻሻያ ቢያደርጉ መልካም ነው። | en_US |
dc.language.iso | en | en_US |
dc.subject | መማሪያ መጽሃፍ፣ ስርዓተ-ጾታ፣ ሚና፣ ውክልና | en_US |
dc.title | በሶስተኛና አራተኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መጻህፍት የስርዓተጾታ ፍትሃዊነት ፍተሻ | en_US |
dc.type | Article | en_US |